የዕለቱ ጥቅስና ጸሎት

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን። ሃሌ ሉያ።
መዝ. )%Ý Ý6

እልልታ የሚያውቅ ህዝብ ምስጉን ነው
አቤቱ ለፊትህ ብርሃን ይሄዳሉ
በስምህም ቀኑን ሁሉ ደስ ይላቸዋል
በጽድቅህም ከፍ ከፍ ይላሉ ፡፡
መዝ.ዳ 98፡13-16

እርዳታ

ለዓላማችን መጠናከር ተባባሪ ይሁኑ!

Amount:


የማኅበሩ ዝግጅቶች

August 2019
S M T W T F S
28 29 30 31 1 2 3
4 5 6 7 8 9 10
11 12 13 14 15 16 17
18 19 20 21 22 23 24
25 26 27 28 29 30 31

 

የፕሮጄክቱ ዋነኛ ዓላማ፦

ሀ. ሰዎች እራሳቸውን ከኤችአይቪ ኤድስ እንዴት መከላከል እንደሚችሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው የስብከተ ወንጌል ትምህርት መስጠት፤ ለዚሁ ተግባር የሚረዱ ከመጽሐፍ ቅዱስ የተውጣጡ መንፈሳዊ እና ትምህርታዊ ምክሮችን በተለያዩ ቋንቋዎች ማስተርጎምና ማሰራጨት፤

ለ. እንደ ክርስቲያንና አንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ በበሽታው የተያዙ ወገኖችን እንዴት መንከባከብ እንደሚኖርብን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስብከት በማድረግ ማስተማርና ማሳወቅ ነው። ከተደረገው የስብከተ ወንጌል እና ስልጠና በኋላ በተደረገ ጥናት ስልጠናውን የወሰዱ ሰዎች ያላቸው ግንዛቤ ትክክለኛ መሆን እንደቻለ እና በተለይም ደግሞ ቫይረሱ በደማቸው ያለባቸውን ወገኖች ማግለል እና የሚያስከትለውን ጉዳት በትክክል መገንዘብ እንዲችሉ ተደርጓል። በፕሮጄክቱ የቅዱሳት መጻሕፍትና የተለያዩ ትምህርታዊ ጽሑፎች ስርጭት ከላይ እንደተገለጸው በዚህ ፕሮጄክት ከልዩ ልዩ የወንጌል ክፍሎች የተውጣጡ የማስተማሪያ ማቴሪያሎች ይሰራጫሉ። በዚሁ መሠረት ፦

  • የደጉ ሳምራዊ የስብከት ማሰልጠኛ ……………………………13,421
  • የሥልጠና ማኑዋል……………………………………………………536
  • “ኃላፊነት ውሰዱ” በሚል የተዘጋጀ ቡክሌት………………1,000
  • ፍሊፕ ቻርት …………………………………………………………192
  • የደጉ ሳምራዊ ቪዲዮ ካሴት ……………………………………100

               በድምር 16,349 ማቴርያሎች ተሰራጭተዋል።