የዕለቱ ጥቅስና ጸሎት

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን። ሃሌ ሉያ።
መዝ. )%Ý Ý6

እልልታ የሚያውቅ ህዝብ ምስጉን ነው
አቤቱ ለፊትህ ብርሃን ይሄዳሉ
በስምህም ቀኑን ሁሉ ደስ ይላቸዋል
በጽድቅህም ከፍ ከፍ ይላሉ ፡፡
መዝ.ዳ 98፡13-16

እርዳታ

ለዓላማችን መጠናከር ተባባሪ ይሁኑ!

Amount:


የማኅበሩ ዝግጅቶች

August 2019
S M T W T F S
28 29 30 31 1 2 3
4 5 6 7 8 9 10
11 12 13 14 15 16 17
18 19 20 21 22 23 24
25 26 27 28 29 30 31

ሀ. የመስሚያ ማዕከላትን በማቋቋም ረገድ፦

ከላይ እንደተገለጸው የእምነት ከመስማት ይመጣል ተግባር በየአብያተ ክርስቲያናቱ ወይንም አመቺ በሆኑ ቦታዎች ሃምሳ ሃምሳ ሰዎችን ያቀፈ ቡድን በማቋቋም የተቋቋሙት ቡድኖች በሳምንት አንድ ቀን ለ30 ደቂቃ በድምጽ የተቀረጸውን አዲስ ኪዳን በማድመጥና ለ15 ደቂቃ ውይይት እንዲያደርጉ በማድረግ ቃለ እግዚአብሔር እንዲደርሳቸው ማስቻል ነው። በዚሁ መሠረት፦ በአዲስ አበባ፣ በባህር ዳር፣ በወሎ፣ በጎንደር፣ በመቱ፣ በደሴ፣ በነቀምቴ፣ በምዕራብና ምሥራቅ ኦሮምያ፣ በድሬደዋ፣ በሐረር ሂርና፥ በመቀሌና አዲግራት በኮንሶ፣ በቤንሻጉል ቤንች 500 የአዲስኪዳን የመስሚያ ማዕከላት እንዲቋቋሙ ተደርጓል።

ለ.አዲስ ኪዳን በድምጽ ማሰሚያ መሣሪያ ስርጭት

ከላይ ለተቋቋሙት የመስሚያ ማዕከላት አገልግሎት የሚውል 2,000 በዘመናዊ ዲጂታል መሣሪያ በተለያዩ ቋንቋዎች የተቀረጹ የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ስርጭት ተደርጓል። የዚህም ዝርዝር እንደሚከተለው ነው።

በአማርኛ ቋንቋ የተቀረጹ አዲስኪዳን ካሴት

በቤንች    ቋንቋ የተቀረጹ አዲስ ኪዳን ካሴት

በትግርኛ ቋንቋ የተቀረጹ አዲስ ኪዳን ካሴት    

በምዕራብ ኦሮምኛ ቋንቋ የተቀረጹ አዲስ ኪዳን ካሴት

በምስራቅ ኦሮምኛ ቋንቋ የተቀረጹ አዲስ ኪዳን ካሴት      በወላይታ ቋንቋ የተቀረጹ አዲስ ኪዳን ካሴት               

           

                                          

ድምር         

350

100

250

100

100

100

 

1,000

በአጠቃላይ ፕሮጄክቱ አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ከ2002 ዓም ጀምሮ ከ6,500 በላይ ማዕከላትን በማቋቋም ለ2,800,000 አድማጮች አገልግሎት ለመሰጠት ተችሏል። አብዛኛዎቹ የዚህ ፕሮግራም ተሳታፊዎች መጻፍና ማንበብ የማይችሉ፤ ማየት የተሳናቸው፤ በማረሚያ ቤቶች የሚገኙ የሕግ ታራሚዎች፤ በተሐድሶ ማዕከላት የሚገኙ የጎዳና ተዳዳሪዎችና ወላጅ አልባ ህጻናት እንዲሁም በስደተኛ ጣቢያ የሚገኙ የጎረቤት አገር ዜጎች ናቸው።