የዕለቱ ጥቅስና ጸሎት

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን። ሃሌ ሉያ።
መዝ. )%Ý Ý6

እልልታ የሚያውቅ ህዝብ ምስጉን ነው
አቤቱ ለፊትህ ብርሃን ይሄዳሉ
በስምህም ቀኑን ሁሉ ደስ ይላቸዋል
በጽድቅህም ከፍ ከፍ ይላሉ ፡፡
መዝ.ዳ 98፡13-16

እርዳታ

ለዓላማችን መጠናከር ተባባሪ ይሁኑ!

Amount:


የማኅበሩ ዝግጅቶች

April 2018
S M T W T F S
1 2 3 4 5 6 7
8 9 10 11 12 13 14
15 16 17 18 19 20 21
22 23 24 25 26 27 28
29 30 1 2 3 4 5

sidama

ላለፉት 17 ዓመታት ሲከናወን የነበረው የሲዳምኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ሥራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ጥቅምት 27 ቀን 2008 ዓ.ም. በከፍተኛ ድምቀት ተመርቆ ስርጭቱ ተጀምሯል። በምረቃው ሥነ ስርዓት ላይ የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች፥ የመንግስት ባለስልጣናት፥ ከልዩ ልዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የተጋበዙ የክብር እንግዶችና በርካታ ቁጥር ያላቸው የክልሉ ተወላጆችና የሲዳምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ምዕመናን ተገኝተዋል። 
 
በዕለቱ ፕሮግራም የማኅበሩ ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ተስፋጽዮን ደለለው ባደረጉት ንግግር ሰዎች በሚረዱበት እና በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው መጽሐፍ ቅዱስን አስተርጎሞና አሳትሞ ማቅረብ ከሁሉ  የከበረ ተግባር እና የላቀ መሆኑን ገልጸው በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ከቆመለት ዓላማ በመነሳት ለሥራው ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ ገልጸዋል።  የእዚህ ሥራ እና ጥረት አካል የሆነው እና ላለፉት በርካታ ዓመታት ሲከናወን የነበረው የሲዳምኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ሥራ ከብዙ ዓመታት ጥረት እና ድካም በኋላ ለፍጻሜ በመብቃቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል። የሲዳማ ብሔር ተወላጆች እና የቋንቋው ተናጋሪዎችን በሙሉ እንኳን ደስ ያላችሁ! ብለዋል። 
 
የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች በየተራ ባደረጉት ንግግር ፥ ቤተ ክርስቲያናት ለተልዕኮዋ መሳካት የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም እና ስርጭት  ያለውን ጠቀሜታ በመግለጽ በተለይ በዘመናችን ያለው ትውልድ በራሱ ቋንቋ የእግዚአብሔርን ቃል አግኝቶ በእምነቱ እንዲበረታ ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸው፥ በሲዳምኛ ቋንቋ የተተረጎመው መጽሐፍ ቅዱስም ለዚሁ ለቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ መሳካት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው እና ለተልዕኳቸው መሳካትም እገዛ እንደሚያደርግላቸው ገልጸዋል። በእለቱም  የታተመው መጽሐፍ ቅዱስ በጸሎት ከተባረከ በኋላ ስርጭቱ በይፋ ተጀምሮ በርካታ ምዕመናን እጅ እንዲደርስ ተደርጓል።

DSC00015 150x150ማኅበሩ በ2014 ዓ.ም. በ18 የትርጉም ፕሮጄክቶች ላይ የተለያዩ ሥራዎችን አከናውኗል። የፕሮጄክቶቹ ስሞችና የተከናወኑት ሥራዎች መጠን በሚከተለው ሰንጠረዥ ተገልጿል