የዕለቱ ጥቅስና ጸሎት

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን። ሃሌ ሉያ።
መዝ. )%Ý Ý6

እልልታ የሚያውቅ ህዝብ ምስጉን ነው
አቤቱ ለፊትህ ብርሃን ይሄዳሉ
በስምህም ቀኑን ሁሉ ደስ ይላቸዋል
በጽድቅህም ከፍ ከፍ ይላሉ ፡፡
መዝ.ዳ 98፡13-16

እርዳታ

ለዓላማችን መጠናከር ተባባሪ ይሁኑ!

Amount:


የማኅበሩ ዝግጅቶች

November 2018
S M T W T F S
28 29 30 31 1 2 3
4 5 6 7 8 9 10
11 12 13 14 15 16 17
18 19 20 21 22 23 24
25 26 27 28 29 30 1

Bible Society of Ethiopia1ራዕያችን

በአገሪቱ ብቁ እና ውጤታማ የቅዱሳት መጻሕፍት ተርጓሚ፥ አታሚ እና አከፋፋይ በመሆን ለእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ቅዱሳት መጻሕፍትን ማዳረስ።

ተልዕኳችን

ከአብያተ ክርስቲያናት እና ከክርስቲያን ድርጅቶች ጋር በመተባበር፤ ለመላው ኢትዮጵያዊያን ቅዱሳት መጻሕፍትን በቀላሉ ሊረዱት በሚችሉት ቋንቋ በማስተርጎም እና በሚያመቻቸው ዓይነትና መጠን በማሳተም፤ ሊገዙ በሚችሉት ዋጋ ወይንም በነፃ በማከፋፈል፥ የአግዚብሔርን ቃል ማቅረብ እና እንዲጠቀሙበት ማበረታታት።

Subkategorieëe

Untitledአንጋፋው የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ከተመሠረተ ዘጠኝ አሥርተ ዓመታት ሊያስቆጥር ማስገምገሙን እንደቀጠለ ነው፡፡ በእነዚህ ዓመታት ጥቂት የማይባሉ ታላላቅ ሰዎች የማበሩን ቦርድ በሰብሳቢነት (ፕሬዝዳንትነት) መርተው አልፈዋል፡፡


ለአብነት ያህል ክቡር አቶ አበበ ረታ፣ አቶ አማኑኤል አብረሃም፣ አቶ አስፋው ተፈራ፣ አቶ ውብሸት ደለኝና አቶ ማርቆስ ገብረማርያም ይጠቀሳሉ፡፡ በዋና ፀሐፊነትም ያገለገሉት ውስጥ አቶ ሚሊዮን በለጠ፣ አቶ ኃይሉ ወ/ሰማያት፣ አቶ ከበደ ማሞና በአሁኑ ወቅት አቶ ይልማ ጌታሁን ይገኙበታል፡፡ እነዚህ ለምሳሌ ህል ይጠቀሳሉ እንጂ በሰብሳቢነትም ሆነ በዋና ፀሐፊነት አመራር በመስጠት ማበሩን አሁን ወደሚገኝበት ደረጃ እንዲደርስ የጣሩ ብዙዎች የሚረሱ አይደሉም፡፡ ይህንንም የማበሩ ታሪክ በመልካም ሁሉ እንደሚያስታውሳቸው አይጠረጠርም፡፡ በቦርድ አባልነት ደግሞ ጊዜአቸውንና ጉልበታቸውን ገንዘባቸውንም ጭምር በመስጠት የማበሩን ዓላ ግቡን እንዲመታ የለፉ ቁጥራቸው እጅግ ብዙ እህቶች እና ወንድሞች የማበሩ ታሪክ አካል ሆነው የቆዩና ያገለገሉ ለአፍታም የሚረሱ አይደሉም፡፡ እነዚ ሁሉ የወቅቱን ተለዋዋጭ ተግዳሮቶች እየተወጡ አስፈላጊውን መስዋዕትነት ሁሉ ከፍለው ማበሩ አሁን ለሚገኝበት ደረጃ አድርሰዋል፡፡ አሻራቸው በጉልህ አሁን ላለው ትውልድ ይታያል፡፡ የአለፉትና ያሉት ሠራተኞችም ለማበሩ ሥራ ያበረከቱት ቅን አገልግሎት ከማበሩ ታሪክ ጋራ አብሮ የተገመደ ስለሆነ ከማኅበሩ መለየት አይቻልም፡፡

አሁን ያለውም የኢትጵያ መጽሐፍ ቅስ ማበር ቦርድና አመራር ማበሩ የተቋቋመለትን ዓላማ ሳያዛንፍ ግብ ለማድረስ ያልተቆጠበ ጥረት ያደርጋል፡፡ የማኀበሩም ዓላማ ታላቁን ተልዕኮ "እንግዲህ ሂዱና  አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችሁኋቸው ደቀመዛሙርት አድርጓቸው፡፡ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍሜ ድረስ ሁል ጊዜ ከናንተ ጋር ነኝ" (ማቴ. @8÷09-@) ያለውን ሕያው ቃል መርህና መሠረት አድርጐ ነው፡፡ ይህም ለኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ላፊነቱን ሰፊ ያደርገዋል፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ ከ*ቋንቋዎች በላይ የበለጸገችና ብዝሐነታችን በዚያው መጠን የሰፋ ስለሆነ በእያንዳንዱ ቋንቋ መጽሐፍ ቅዱስን ተርጉሞና አሳትሞ ለማዳረስ ያለው ተግዳሮት ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ እስካሁን ሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ የተተረጐመላቸው እና የታተመላቸው በሰባት ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ፥ በኦሮምኛ፥ በወላይትኛ ፥ በጉራጊኛ፥ በአኝዋክኛ በትግርኛ እና በሲዳምኛ ሲሆን የቀረው ሥራ ምን ያህል እንደሆነ አንባቢው መገንዘብ ይችላል፡፡

ይሆን እንጂ የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ብቻውን ስላልሆነና የመላው ሕዝበ ክርስቲያን ጸሎትና ድጋፍ አብሮት ስላለ ኃላፊነቱን በቀላም ባይሆን እንደወጣ እናምናለን፡፡ እንደነህምያም "የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን" ብለን ቃል እንደገባለን፡፡

በክርስቶስ በሰማያዊ ፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።” (ኤፌ. 1÷3)

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

ተስፋጽዮን ደለለው (ዶ/ር)

የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ቦርድ ሰብሳቢ